የኩክ የለሽ ማርያም ቤተክርስቲያንን ወደ ነበረበት ለመመለስ እና እድሳት ለማድረግ በምናደርገው የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ የበኩሎዎን ይወጡ!
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ የምትገኘውና በድንቅ ተዓምራቷና ፈዋሽነቷ በአለም የምትታወቀው ታሪካዊቷ የኩኬለሽ ቅድስት ማርያም ገዳም፤ በአባ ኃ/ጊዮርጊስ አማካኝነት 14 አመታትን ጊዜ ፈጅቶ በ4 ፍልፍል ዋሻ አብያተ ክርስቲያናትና በ1 ቤተክርስቲያን እንደተገደመች ይነገራል።
በንግሥ ክብረ በዓሉና በጉባኤው በመገኘት፣ እንዲሁም የቀጥታ ሥርጭቱን በመደገፍና ለ አለም እንዲደርስ በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ገዳሟ ጥሪዋን ታቀርባለች።
በመላው አለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች፤ የታሪካዊቷ ቅድስት ኩክ የለሽ ማርያም ገዳም ወዳጆችና ቤተሰቦች፣ በቅድሚያ በፈጣሪ ሥም የከበረ ሠላምታዬን አቀርባለሁ።
በረከትዋ በአለም የተነገረላት በምልጅዋና በፈዋሽነቷ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን የመሠከሩላት እመቤታችን ኩክ የለሽ ማርያም ገዳም የተደቀነባትን የመሰንጠቅና የመሬት መደርመስ አደጋ በልጆቿ ትብብር ይቀለበስ ዘንድ ሁላችንም ርብርብ እንድናረግ በታላቅ ክብርና አደራ እጠይቃለሁ።
ሠላም ፍቅርና መተሳሰብ ለሀገራችን ይሁን።